• መእተዊ
  • ዜና
  • ፅሑፍ
  • ቪድዮ
  • ቋንቋ | Language
    • English
    • አማርኛ
መተግበሪ የዉርዱ
Facebook Twitter Telegram YouTube Instagram
  • ብዛዕባና
  • ይርከቡና
  • ኣወፍዩ
እዋናዊ
  • Some of the Catholic Leaders in Ethiopia: Agents of Genocide or Agents of Peace?
  • ወገንተኛው፣ መርህ የለሹና ከጅምሩ የከሸፈው የአፍሪቃ ሕብረት ሽምግልና በኢትዮጵያ
  • Aerial bombardment of Mekelle
  • Weekly Briefing No. 10
  • Abiy Ahmed Government Vs Mengistu H/Mariam Government of Ethiopia
  • የትግራይ ህዝብ ጥያቄ ሂሳብ ከማወራረድ በላይ መሆን አለበት
  • Amhara Elites’ Further Military Conscription is More Proof of the Elite’s ‘Hegemonic’ Ambition for Territorial Expansion
  • የመጨረሻው ምዕራፍ መጀመርያ
  • The Alula-Amputated-Eritrean POW Story
Facebook Twitter Telegram YouTube Instagram
ደደቢት ሚድያ ደደቢት ሚድያ
  • መእተዊ
  • ዜና
  • ፅሑፍ
  • ቪድዮ
  • ቋንቋ | Language
    • English
    • አማርኛ
ደደቢት ሚድያ ደደቢት ሚድያ
Home»ወቕታዊ»የመጨረሻው ምዕራፍ መጀመርያ

የመጨረሻው ምዕራፍ መጀመርያ

ወቕታዊ July 31, 20214 Mins Read
Shares
በአባይ ግደይ

የትግራይ ህዝብ ራስን የመከላከል ጦርነት በወሳኝነት ወደ መጨረሻው የድል ምእራፍ እየተሸጋገረ እንደሆነ ወዳጅም ጠላትም የተረዳው ይመስለኛል።

ራስን በመከላከልና ኃይሉን በማጥናከር ላይ የነበረው የትግራይ መከላከያ ኃይል (TDF) “ሀ” ብሎ በጀመረው የአሉላ አባነጋ የማጥቃት ዘመቻ የስበት ማእከል የሆነችውን የትግራይ ዋና ከተማ መቐለን ነፃ አውጥቶ አለም በትግራይ ሃይሎች ያለውን ግምት አስቀይሮታል።

በትግራይ እናቶች የተሰየመዉ ሌላኛው የማጥቃት ውሎም በደቡብ ትግራይ ወሳኝ የተባለው የቆቦ መስመር በጣጥሶ ከወደ ደቡብ ምስራቅና ሰ/ምእራብ እየገሰገሰ ይገኛል።

እነዚህ ወታደራዊ ድሎች በበሳል የፖለቲካ አመራርና ወታደራዊ ስትራተጂ የሚመሩ: ዋና አላማቸው ወራሪው የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና የተሰፋፊው የአማራ ሃይልና ረዳት የየክልሉ ጀሌዎች ከመላው ትግራይ ጠራርጎ ማውጣት ብቻ ሳይሆን: ዳግም አንሰራርተው እንዳይመለሱ በያሉበት ለመድቆስም ጭምር ነው።

አሁን በሚያስገርም ፍጥነት በአፋር መስመር፣ በደቡብና በሰ/ምእራብ ትግራይ እየተካሄደ ያለው የነፃነት ትግል በአዲስ አበባ መንግስትና በአለም ህብረተሰብ እየፈጠረ ያለው አዲስ ስጋት እንዴት ይስተናገዷል የሚለው ጥያቄ ለማንሳትና የግል አስተያየት ለመሰንዘር ነው።

ትላንትና ሲፎክርና ፎካሪውን ሲያጅብ የነበረው የህብረተሰብ ክፍል ምን እየሆነ ነው ያለው? ምንስ ሊያጋጥም ይችላል? እስቲ በመሬት ላይ ያለውን እውነታና አንድምታው እናስቀድም።

የኃይል አሰላለፉ ሙሉ በሙሉ ተቀይሯል። የትግራይ የመከልከያ ሃይል (TDF) የኢትዮጵያ መከላከያን በወሳኝነት አሸንፏል።

የአማራ ተስፋፊ ሃይል በትግራይ መሬት ላይ ያሰፈራቸው: ስማቸው ቀይሮ ለኢንቨስተሮች የቸረቸራቸው የትግራይ ይዞታዎች ይዞ መቆየት ይቅርና በህይወት ለማምለጥም ጊዜው ጨልሞበታል።

የኤርትራ ሰራዊትም እንደነበረው የኢትዮጵያ ሃይልን ሊመራ ይቅርና ለራሱ ሽሽቱን ለማሳመር ገሽሽ ብሎ እየተጠባበቀ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ በኩል በአዲስ አበባ የጁቡቲ መስመር ሊቆረጥ ነው ተብሎ ገንዘብ ያለው ሁሉ ራሱንና ልጆቹን ለማሸሸ ሲጨናነቅ: ሌላው ትግራይ ስተወረርና በውስጥና በውጭ ኃይሎች ስትደፈር ያጨበጨበው አሁን ደግሞ አደባባይ ላይ ወጥቶ ከተሸነፈውና ከተማረከው መከላከያ ጎን እንሰለፋለን ሲል ግራ መጋባቱን ይገልፃል።

በኦሮሞ ሃይሎች የትጥቅ ትግሉ እየገፋ: በሌሎች ክልሎች ደግሞ አዳዲስ የትጥቅ ትግል ጀማሪዎች ብቅ ብቅ ማለት ጀምሯል። የ1983ዓ.ም. ኢህአዴግ አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ሲቃረብ የነበረው ሁኔታ እንዳለ እየተደገመ ነው።

የመንግስቱ ዘመን ሊያበቃ ቀናት ሲቆጠሩ የነበረው ሽርጉድ አሁንም አለ። የመሪዎች ንግግሮች ሁሉ ከዚያው ዘመን የተቀዱ ይመስላሉ። መንግስቱ ወደ ዝምባብዌ ሲያመራ አዲስ መሪ ጀነራል ተስፋየ ገ/ኪዳን ሲሾሙ: የኢህአዴግ ሰራዊት ሲጠጋ የዩኑቨርስቲ ተማሪዎች ሁሉ አዲስ አበባን ለመከላከል ወደ ስልጠና ሲወርዱና ስልጣናቸው ሳይጨርሱ ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጠጠርና እነሱ ወደ ኬንያ ሲፈረጥጡ የነበረው ትእይንት ሁሉ አሁንም አለ።

ታዲያ የመጨረሻው ምዕራፍ መጀመሪያ መሆኑን በምን እንለካው ቢባል፥

1. ሽንፈት ላለመቀበል አሁንም ህዝቡን ማታለልና እንደ ዱቄት በኗል ያሉትን ህዝብ መልሰው የውስጥና የውጭ ሃይሎች ወረውናል በሚሉ ቃላት እያሽሞነሞኑ ማስታወስ የተሳነው (short memory ላሉት) ህዝብ መልሰው “አለን”፣ “አልተማረክንም”፣ “ፎቶሾፕ ነው” እያሉ ይነግሩታል። ህዝቡም ጭብጨባው አልነሳቸውም። የትግራይ ህዝብና ወዳጆቹ ግን በሬሳ ሳጥን ላይ ተጋድሞ እንደሞፈክር መሆኑ በሚገባ ይረዱታል። የአብይና አጫፋሪዎቹ እጣ ፈንታ እየታወቀ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ አብሮ ለመጥፋት መወሰን ነው። ሁሉም መሪዎች ተሽንፈናል ከማለት “አዲስ አበባን” ለመከላከል ሲባል ከመከላከያ ጎን ቁሙ ብለው የኦሮሞ ሰንጋዎች ከወደ ጎንደር አደርሷል።

በትግራይ ጦርነት ዉስጥ የተማረኩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ማረፍያ ቦታቸዉ ሲጓጓዙ [Image credit: The Telegraph]

2. የትግራይ ህዝብ ሰራዊታችን ወግተዋል የሚለው የአብይና የአማራ ክልል መሪ ሌላኛው የክተት አዋጅ ነው። የዚህ አዋጅ እንድምታ ህዝቡ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እንዲያጠቃ የሚያነሳሳ የዘር ማጥፋቱ ምዕራፍ ማገባደጃ መሆኑ ነው። ትግራይ ዉስጥ በመሬትና በስማይ ደብድበው የገደሉትና ያቆሰሉት ሳይበቃቸው ሁሉም ነገር ዘግተው ህዝቡ እንዳለ በረሃብ እንዲያልቅ ያደረጉት ጥረት ሁሉ በጀግናው የትግራይ መከላከያ ሃይል እየከሸፈ መሆኑን ሲያውቁ በኢትዮጵያ የቀረውን የትግራይ ተወላጅ በየቀኑ በአፈሳ እያሰሩና ወደ ማይታወቁ ቦታዎች እያፈኑ በመዉሰድ ለመበቀል የሚደረግ ሙከራ ነው። ይህ አደገኛ አካሄድ ህዝቡ ካላስቆመው እዳው ከባድ ነው።

3. በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዘግይቶም ቢሆን አንዳንድ የሚያበረታቱ አስተያየቶችና መግለጫዎች ማውጣት ጀምሯል። ነገር ግን ዘግይተዉም ቢሆን አገርና ህዝብ የሚታደጉ እውነታዎችን ያነገቡ አይደሉም። በትግራይ ላይ የደረሰውን በደልና ግፍ በተራ ሽምግልና የሚፈታ የእርስበርስ ግጭት አይደለም። የተቀነባበረ አለም-አቀፍ ዘመቻ ነው። የሚቀርቡት የመፍትሄ ሃሳቦች ለደረሰው ችግር የሚመጥኑ አይደሉም። በቅርቡ “concerned citizens” በሚል የተሰጠው የግልግል/ድርድር መነሻ ሃሳብ ብዙውን የትግራይ ህዝብ አስቆጥቷል። ቢያንስ ቢያንስ የአማራ ተስፋፊ ሃይል ተሳስቷል ብሎ አይቀበልም። ሁሉም ገዳይና ሟች እኩል በማስቀመጥ ዳርዳሩን ብቻ በማር በመቀባት መርዙን ለመደበቅ የሞከረ ፅሁፍ ነበር። እንደነዚህ አይነት ሙከራዎች አብይን በስልጣን ለማቆየት ከመመኮር የዘለለ ለመሰረታዊ ችግር መፍትሄ የሚያመጡ አይደሉምና ወቅቱን የጠበቀ ሌላ ተከታታይ መግለጫ እንጠብቃለን።

4. የአለም አቀፍ ህብረተሰብ አብይን በስልጣን ለማቆየት የ8 ወራት ከንቱ ጥረት ሲያደርድ ቆይቷል። አብይንም ማቆየት አልቻለም፤ የትግራይ ህዝብም በጊዜው እርዳታ አልደረሰለትም። ሁለት ስህተት ነው የተፈፀመው። የትግራይ ህዝብም ሁለቴ ነው የተጎዳው። አሁንም የትግራይ ህዝብና ሰራዊት ተገዶ የጠላትን እግር ተከትሎ በሚሰነዝረው የማጥቃት እርምጃ የተለያዩ ስሜቶች እየተፈጠሩ ነው። ሁላችንም ለአለም ህብረተሰብ አስቸኳይ መልእክታችን ማድረስ ይኖርብናል። አለማችን ካለፉት 8 ወራት የአብይና ኢሳያስ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተግባር መማር የሚችለው አሁን በመጨረሻው ምዕራፍ የተሸነፈው የአብይ ቡድን ቶሎ ቦታውን ለቆ ለፍርድ እንዲቀርብ በመተባበርና በሰላማዊ የትግራይ ተወላጆች ላይ እያደረሰ ያለውን ጥቃት እንዲቆም በመከላከል ነው።

በመጨረሻም ተወደደም ተጠላም የትግራይ ሃይል የአከባቢው ወሳኝ ኃይል ወደ መሆን ተሸጋግሯል። “የማይቀርልህ እንግዳ አጥበቀህ ሳም” በትግርኛ “ዘይቐርየካያ ጋሻስ አጥቢቕካ ስዓሞ” እንደሚባለው ለማይቀረው እንግዳ በሰላም ተቀብሎ ከማስተናገድና በቀጣዩ የኢትዮጵያ ጉዳይ ተወያይቶ ከመፍታት ወጪ መንፈራገጥ ከመላላጥና ጥፋት ከመጨመር ሌላ ለውጥ አያመጣም። የሰው ልጅ ትልቁ ችሎታ ወድቆ መነሳት መቻልና ከስህተት መማር ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በ30 አመታት ሰላምና እድገት ወይም በ3 አመታት የሲኦል ጊዜ ካልተማረ ያለው አማራጭ ኢትዮጵያዊ አለመሆን ነው። የትግራይ ህዝብ እንኳ ትግራዋይ መሆን የሚመርጥ ይመስለኛል።

ቸር ያሰማን!

አባይ ግደይ


Please note that the opinions expressed in this article are the author’s opinions and do not necessary represent Dedebit Media’s position on the issue, unless explicitly expressed.

If you have any constructive comments, please contact us via dedebitmedia2020@gmail.com

Shares
Post Views: 335
Previous ArticleThe Alula-Amputated-Eritrean POW Story
Next Article Amhara Elites’ Further Military Conscription is More Proof of the Elite’s ‘Hegemonic’ Ambition for Territorial Expansion

ተዛመድቲ

Some of the Catholic Leaders in Ethiopia: Agents of Genocide or Agents of Peace?

ፅሑፋዊ ትንተና October 19, 20216 Mins Read

Weekly Briefing No. 10

ፅሑፋዊ ትንተና October 14, 20218 Mins Read

Abiy Ahmed Government Vs Mengistu H/Mariam Government of Ethiopia

ፅሑፋዊ ትንተና August 26, 20215 Mins Read
Add A Comment

Leave A Reply Cancel Reply

እዋናዊ

Some of the Catholic Leaders in Ethiopia: Agents of Genocide or Agents of Peace?

ፅሑፋዊ ትንተና October 19, 20216 Mins Read

ወገንተኛው፣ መርህ የለሹና ከጅምሩ የከሸፈው የአፍሪቃ ሕብረት ሽምግልና በኢትዮጵያ

ፅሑፋዊ ትንተና October 19, 20219 Mins Read

Aerial bombardment of Mekelle

ፅሑፋዊ ዜና October 18, 20211 Min Read

Weekly Briefing No. 10

ፅሑፋዊ ትንተና October 14, 20218 Mins Read
ኣብ ፌስቡክ ይርከቡና
Facebook page
ኣብ ትዊተር ይስዓቡና
Twitter
ብዛዕባና

ደደቢት ሚድያ ጥቕምን ክብርን ትግራይ ኣብ ምሕላው፣ ዝተዛብዐ ታሪኽ ኣብ ምስትኽኻል፣ ዝተወሰደ ቅርሲ ኣብ ምምላስን ንቐፃሊ ውሕስነት ትግራይ ኣብ ምርግጋፅን ጠንኪሩ ዝሰርሕ ሚድያ እዩ፡፡

ደደቢት ሚድያ ብቋንቋታት ትግርኛ፣ ኣምሓርኛን ኢንግሊዝኛን መደባት የዳሉ።

እዋናዊ

Some of the Catholic Leaders in Ethiopia: Agents of Genocide or Agents of Peace?

ፅሑፋዊ ትንተና October 19, 20216 Mins Read

ወገንተኛው፣ መርህ የለሹና ከጅምሩ የከሸፈው የአፍሪቃ ሕብረት ሽምግልና በኢትዮጵያ

ፅሑፋዊ ትንተና October 19, 20219 Mins Read

Aerial bombardment of Mekelle

ፅሑፋዊ ዜና October 18, 20211 Min Read
ቤተሰብ ደደቢት ሚድያ ንምዃን ይመዝገቡ

መተግበሪ የዉርዱ
Facebook Twitter Telegram YouTube Instagram
  • ብዛዕባና
  • ይርከቡና
  • ኣወፍዩ
© 2023 ደደቢት ሚድያ

Type above and press Enter to search. Press Esc to cancel.